ነፃ የመፅሃፍ ቅዱሳዊ ዕብራይስጥኛ የቪድዮ ትምህርት - መግቢያ
የየትኛውም ቋንቋ ተናጋሪ ቢሆኑ የመፅሃፍ ቅዱሳዊ ዕብራይስጥኛን ለማንበብ በዚህ ነፃ የቪዲዮ ትምህርት መማር ይችላሉ! የዕብራይስጥኛ ቋንቋ ምንም አይነት ዕውቀቱ ለሌላቸው እንዲሁም ከዚህ በፊት ዕብራይስጥኛን ላጠኑ ሰዎችም ይሆናል! አንድ ህፃን ልጅ አፍ የሚፈታበትን ቋንቋ በሚማርበት መንገድ እንዲማሩ በሚያስችል መንገድ እናስተምሮታለን። ለብዙ ሰዎች ዕብራይስጥኛ መማር ውድ፣ አስቸጋሪና ተስፋ አስቆራጭ ነው። ያን መቀየር እንፈልጋለን። በቪዲዮቻችን በመማር ከሚያገኟቸው ጥቅሞች ውስጥ የተወሰኑት እነዚህ ናቸው፤
✓ ነፃ! ለሁሌም ምንም አይነት ምዝገባ የለም። ምንም አይነት የሙከራ ጊዜ አያስፈልግም። ✓ አንድ ህፃን እንደሚማርይማሩ፡በማየትናበመስማት። ✓ መጨናነቅ የለም። በራስዎ የመማር ፍጥነት ይሂዱ እና ይደሰቱ! ✓ ሊያስታውሷቸው የሚገቡ የህግጋት ዝርዝር የለም። ✓ ምንም አይነት መፅሃፍ አያስፈልግም። ✓ በሁሉ ምቋንቋዎችና ሃገራትይሰራል። ✓ ለህፃናትና እና በቤት ውስጥ ለሚማሩ ልጆች ምርጥ ነው።
መፅሃፍ ቅዱስ መጀመሪያ በተፃፈበት ቋንቋዎች በጥልቀት በማጥናት በአንድነት ቤተክርስቲያን (የክርስቶስአካል) በጥበብ ማደግ እንድትችል እባክዎይህን ነፃት ምህርት ለጓደኞችዎ በማጋራት ይተባበሩን! እዚህ ጋር የመጀመሪያውን ትምህርት በመማር መጀመር ይችላሉ። https://youtu.be/y640-FIpxQs በዚህ የአጫዋች ዝርዝር ላይ ሁሉንም ትምህርቶች በቅደም ተከተል ማግኘት ይችላሉ። https://www.youtube.com/playlist?list... የዕብራይስጥኛ አስተማሪ ከሆኑና ሌሎች ብዙ ነፃ የማስተማሪ ያመሳሪያዎችን ከእኛ ጋር በትብብር ለመስራት ከፈለጉ፣ እባክዎን እኛን ያናግሩን።
Many thanks to Ephraim Solomon for his help with this video!
እንደዚህ አይነት ሌሎች ቪድዮዎችን መመልከት ከፈለጉ፣ እዚህ ጋር አገልግሎታችንን ይደግፉ። https://freehebrew.online/give
Transcript